ለክላስተር ማዕከል አስተባባሪዎችና ለጣቢያ ኃላፊዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ

ዕረቡ በ15/09/2010 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ተመልምለው ለ11ዱም ክልሎች ለተመደቡ 138 የክላስተር ማዕከል አስተባባሪዎች እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ አርብ በ17/09/2010 ዓ/ም ከአዲስ አበባ 11ዱም ክፍለ ከተሞች ለታዳጊ ክልሎች /ለአፋር፣ ለቤኒሻንጉል፣ ለሶማሌና ጋምቤላ/ ለተመለመሉ 300 የጣቢያ ኃላፊዎች በኤጀንሲያችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ አጠቃላይ የፈተናው ሂደት ምን መልክ እንደሚኖረውና እና ያለባቸውን ኃላፊነት በተመለከተ በኤጀንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በአቶ አርአያ ገ/እግዚአብሄር እና በፈተና ዝግጅትና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ አረጋ ማማሩ አማካኝነት ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ እንዲሰማሩ ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል የቱሌቪዥን ጣቢያ ተመሳሳይ ኦረንቴሽን የተፈታኝ ተማሪዎችን ግዴታና መብት ባካተተ መልኩ በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡