ማስታወቂያ ከድጋሜ ሰርተፍኬትና የትምህረት ማስረጃ ማረጋጫ ቡድን
ለጤና ተመራቂ የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ ለምትመዘገቡ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለምትፈልጉ ተገልጋዮች በሙሉ፤
እንደሚታወቀው እስካሁን ድረስ የማረጋገጫ አገልግሎት በግል እየመጣችሁ ስናስተናግድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የሚመጣው ተገልጋይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ አስቸጋሪ ስለሆነ አሰራሩን መቀየር አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ለተወሰነ ወራት ስራውን ማስቆማችን ይታወቃል፡፡
ሆኖም ተፈታኞች ማስረጃ ማረጋገጥ ስላለበት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት መሰረት በግለሰብ ደረጃ አረጋግጦ ለግለሰቡ መስጠቱን በመቀየር ወይም በመተው እንዲረገጋጥለት በፈለገው ተቋም ለመላክ ስለተስማማንና ስራው መሰራት ስላለበት ተቋሙ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደምትስተናገዱ እያሳሰብን መስተናገድ የምትችሉት፤
1ኛ በ email online በመላክ፤
2ኛ በተማራችሁበት ኮሌጅ በጋራ በመሰባሰብና በተወካይ በላክ የምናስተናግድ መሆኑን ስንገልፅ፤
በ email online ለሚልኩ ተገልጋዮች
- የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኮፒ ስካን ተደርጎ፤
- አገልግሎት ክፍያ የተከፈለበት የባንክ ደረሰኝ ስካን ተደርጎ፤
በጋራ ተሰባስቦ በተወካይ ለሚልኩ ተገልጋዮች
- የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኮፒ፤
- ከተቋሙ የተፃፈ የድጋፍ የውክልና ደብዳቤ፤
- የተማሪዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ፤
ማሳሰቢያ፡-
- በ email online የመላኪያ አድራሻ studentneaea@gmail.com መሆኑ ይታወቅ፤
- በግሉ በተናጠል በአካል የሚመጣ ተገልጋይ የማናስተናግል መሆኑ፤
- በ email online የላከ በተወካይ ወይም በአካል በድጋሜ መላክ የለበትም፤
- ውጤቱን ወደ የቀድሞው ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ (HERQA) የምንልክ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- በቀኑ የተሰራውንና የተላከውን ዝርዝር በድረ-ገጻችን የምንልክ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ስማችሁ የተላከ መሆኑን ለማረጋገጥ በድረ-ገፅ neaea.gov.et ገብታችሁ ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውንም ጥያቄ የሚቀበልና ምላሽ የሚሰጥ አካል ስለተመደበ በተገለፀው ኢ-ሜይል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ኮፒ 50 ብር ሂሳብ የ10ኛ እና የ12ኛ ከሆነ ደግሞ 100 ብር በአካባቢያችሁ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መክፈል የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- የመክፈያ አካውንት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000003784758 መሆኑን እገልፃለን፡፡
- በኢ-ሜይልም ሆነ በተወካይ የሚመጡ ሰነዶች ተረጋግጠው የሚሰጠው ለግለሰቡ ሳይሆን ለተቋሙ በቀጥታ የምንልክ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የማረጋገጫ አገልግሎት የሚሰጠው ከመጋቢት 6 እስከ ሚያዚያ አጋማሽ ድረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡