በኦንላየን ምዝገባ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክርና ስልጠና ተካሄደ

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እስካሁን ይሰራበት የነበረውን የተፈታኞች ምዝገባ አሰራር ለማዘመን የኦንላየን ምዝገባ ( Online Registration) የአሰራር ስርኣትን ለመተግበር ከክልል የፈተና ክፍል ኃላፊዎች፤ ከክልል የፈተና ጉዳይ አስፈፃሚዎች እና የክልል የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለተውጣጡ አካላት በአዳማ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ አሰራሩ ባለፉት ሁለት አመታት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በሙከራ የተተገበረ ሲሆን ውጤታማ በመሆኑ በዚህ አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በኩሪፍቱ ሆቴል ዛሬ የተጀመረ ሲሆን በነገው እለትም ይቀጥላል፡፡