ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል መርህ በተዘጋጀው የትምህርት ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ የኤጄንሲው ሰራተኛ በመገኘት አረንጓዴ አሻራውን አሳረፈ

በተለምዶ የትምህርት ዘመኑ የመጨረሻ ቀን በሆነው ሰኔ ሰላሳ (30) የትምህርት ሚኒስቴር እና የኤጄንሲው ከፍተኛ አመራራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በኤጄሬ ከተማ በሚገኝ በአንቦ ዩኒቨርሲቲ የዕጽዋት ማዕከል የተለያዩ አገር በቀል ዛፎች ተተከሉ፡፡
በመርሀ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስተሩ ዶ/ር ኢንጂኔር ጌታሁን መኩሪያ እና የአንቦ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸውም የሚተከሉትን ሀገር በቀል ዕጽዋት መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ እንደሚገባ አጽዕኖት ሰጥቷል፡፡ በተለይ ዩኒቨርሲተው ስፍራውን ከሰው እና ከእንስሳት ንክኪ የተጠበቀ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
በማዕከሉ የተገኘው ሰራተኛም የትምህርቱ ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ላይ በመሳተፋቸው በጣም መደሰታቸውን ገልጸው ለለተከሉት እጽዋትም እንክብካቤ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ በመጨረሻም ሰራተኛው በባለሙያ በተሰጠው መመሪያ መሰረት ሀገር በቀል እጸዋቱን በተገቢው መልኩ ተክሏል፡፡