የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሠራተኞች ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ቁሰቁሶችን አበረከቱ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰሜኑ ግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን በዛሬው እለት የተለያዩ ቁሰቁሶችን አበረከቱ፡፡ የአገልግሎቱ ተወካይ ሠራተኞቹ የተለያዩ ጉዳት የደረሰባቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሻዎች ጎብኝተዋል፡፡ በተተደረገው የልገሳ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ እናንተ የኛ ጀግኖች ናችሁ፡፡ እናንተ በከፈላችሁት መስዋአተነት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም አየር እንተፈሰ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከሃዲው፣ ባንዳውና አሸባሪው የህውሃት ሽፍታ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ በግንባር ለሚዋደቁት ጀግኖቻችን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም አገልግሎቱ በጦር ግንባር ላይ ለተሰማሩት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለክልል ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሻዎች እና ፋኖዎች የሚያደረገውን ልገሳ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡