የትምህርት ምዘናና ፈታናዎች አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ “በሥነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጲያ” (Ethical Leadership for Corruption free Ethiopia) በሚል መሪ ቃል አክብሯል፡፡
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ሙስና እንደ ሀገር ከፍተኛ ነቀርሳ እየሆነ መምጣቱ በዚህ ጉዳይ ላይ የአገልግሎቱ ሠራተኞች በሚቀርበው የግንዛቤ ማስጫበጫ ሠነድ በሚገባ በመከታተት በውይይት እንዲያዳብሩት አቅጣጫ አስቀምጣዋል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሠነዱም በኤጀንሲው የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ደሱ እጅጉ ቀርቦ በአገልግሎቱ ሠራተኞች ከፍተኛ ውይይቶች ተደርጎበትና የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ከተነሱት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ዋነኛው የቀረበው ሠነድ ከጽንሰ-ሃዛብ በዘለለ የአገልግሎቱን ተጨባጭ ሁኔታን ያከተተ ቢሆን የተሻለ የውይይት መድረክ ሊሆን ይችል እንደነበረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡ ከአገልግሎቱ ሠራተኞች ለተነሱት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገቢ ምላሽ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ተጠናቋል፡፡