በዛሬው እለት በሀገራችን ደረጃ ለ16ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ “የጸረ-ጾታዊ ጥቃት “ሰላም ይስፈን” በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም!” “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚሉ መሪ ቃል በአገልግሎታችን በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉም ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በመከበር ላይ የሚገኘውን የነጭ ሪቫን ቀን አስመልክቶ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በመላው ህብረተሰብ ሊወገዝ የሚገባው መሆኑን የሚያስገነዝብ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገጠማት የህልውና ዘመቻ ጋር በተያያዘ በአየአውደ ውግያው ሴት እህቶቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ ልጆቻችን፣ እናቶቻችን እያከፈሉ የሚገኘውን ምስዋትነትና እየሠሩ የሚገኘውን ጀብድ ጠቅሰዋል፡፡ ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ ያሉ አስከፊ እውነታዎችን ሊለወጡ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም በአግልግሎቱ
የሴቶች እና ህጻናት ዳይሬቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ዲላሜ ደመቀ እለቱን አስመልክተው አጭር መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ወንዶች ጾታዊ ትንኮሳ እንዳያካሄዱ፣ ጾታዊ ትንኮሳ ሲፈጸም ከተመለከቱ እንዲያጋልጡ ቃል በማስገባት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡