የ2010ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለሰራተኛ ቀረበ

በዛሬው ዕለት በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ የኤጀንሲያችን የ2010 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በኤጀንሲው ፕላን ፕሮግራምና በጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ሊቀመኳስ ኪዳኔ ለመላው የኤጀንሲው ሰራተኞች ቀርቧል ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ ኤጀንሲው በግማሽ ዓመቱ ያከናወናቸውን ሰፋፊ ስራዎች ሪፖርት በአጭሩ እንደሚቀርብ አስገንዝበው ወደ ሪፖርቱ ተገብቷል፡፡
ሪፖርቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ እስከ ትግበራ ምዕራፍ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎች፣ እንዲሁም በአሰራር ሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው የቀረቡ ሲሆን ሪፖርቱን ተከትሎ ሰራተኞች ሊስተካከሉ ይገቧቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ በመስጠት የስብሰባው ማጠቃለያ ሆኗል፡፡