የውጤት መዛባትን የሚፈጥሩ ዋና ዋና መንስኤዎች

በአሁኑ ሰዓት ኤጀንሲያችን እያስተናገዳቸው ካሉ ቅሬታዎች መካከል አንዱ ውጤቴ ትክክል አይደለም ደግሞ ይታይልኝ የሚል ነው፡፡
አብዛኛው ጊዜ የውጤት መዛባት የሚፈጠርባቸው ምክንያቶች ዋና ዋና የስህተት መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 • ተማሪዎች በፈተና ወቅት ጭንቀት (Tension) ውስጥ ገብተው ለምሳሌ ጥያቄዎች 60 ቢሆኑ የአርባኛውን ጥያቄ አርባ አንደኛው ላይ ቢያደርግ ከዚያ በታች ያሉ ጥያቄዎች መልስ በሙሉ መሳት፣
 • የት/ቤት መለያ ኮዳቸውን በትክክል አለማጥቆር፣
 • የተሳሳተ የመፈተኛ ቁጥር መፃፍና ማጥቆር፣
 • የመልስ አሰጣጥ ላይ በፊደሎች መካከል ማጥቆር፣
 • ፊደሎችን የያዘውን ሳጥን ከማጥቆር ይልቅ ምልክት ብቻ አድርጎ ማለፍ
 • የመልስ መስጫው ላይ ፊደሉን የያዘውን ሳጥን አድምቆ ከማጥቆር ይልቅ
  1. በጣም ፍዝዝ አድርጎ ማጥቆር፣
  2. ፊደሉን ብቻ ለይቶ ማጥቆር፣
 • በመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የተለያዩ ፅሁፎችን መፃፍ፣
 • የመልስ መስጫ ወረቀቱን በላብ ማቆሸሽ፣
 • በመልስ መስጫ ወረቀት ላይ ወደታች የቁጥሩን ቅደም ተከል ጠብቆ ከመስራት ይልቅ ወደ ጎን መልሱን መስራት፣
 • የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ እስኪሪብቶ መጠቀም፣
 • የት/ት ዓይነት መለያ ኮድ በተገቢው የት/ት ዓይነት አለማጥቆር፣
 • ተገቢውን የቡክሌት ኮር አለማጥቆር፣
 • ለአንድ ጥየቄ ከአንድ በላይ መልስ ማጥቆር፣
 • የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪ ሆኖ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶችን መፈተን እና በመሳሰሉት ችግሮች ያለተጠበቀ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል ታሳቢ ሊሆን ይገባል፡፡

እነዚህን ችግሮች ወደፊት እንዳይከሰቱ የፈተና ኦሬትኔሽን በሚሰጥበት ወቅት በአግባቡ መከታተል ችግሩን የሚቀርፍ መሆኑን ኤጀንስያችን ያሳውቃል፡፡