ኦንላይን ሬጅስትሬሽን

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ የቴክኖሎጂ እድገትን በተከተለ መንገድ አሰራሩን በየዘርፉ በማዘመን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባን ኮምፒዩተራይዝድ (Online Registration System) የተከተለ የምዝገባ ስርዓት ለማከናወን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ በአዲስ አበባ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በ2009 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ በሚገኙ የምንግስትና የመንግሥት ባልሆኑ የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች የመደበኛ፣ የማታና የግል ተመዝጋቢዎችን በኦንላየን ሬጅስትሬሽን ስርአት እንዲያከናወኑ ተደርጓል፡፡

ከዛ ቀደም ብሎ በኤጀንሲው የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል የምክክር ጉባኤ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዚህ የምክክር ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ፈተና ክፍል ኃላፊ፣ የየክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የፈተና ክፍል ኃላፊዎች፣ የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ከኤጀንሲው የሚመለከተቸው የሥራ ክፍሎች ተገኝተው ነበር፡፡ 

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አበራ የምክክር መድረኩ የተዘጋጀው በ2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደረጃ ምዝገባው በOnline Registration System እንዲከናወን በመታቀዱና ከምዝገባው በፊት የሚመለከታቸው አካላት በተግባሩ ዙሪያ የጋራ መግባባት እንዲኖራቸው ታስቦ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም የዚህ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች ለOnline Registration System ስኬታማነት የሚኖራቸው ተሳትፎና ድጋፍ የላቀ በመሆኑ የምዝገባውን ሂደት ባሉበት በቅርበት በመከታተልና ለሚከሰቱ ምንም ዓይነት ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ከኤጀንሲው ጋር ተቀራርበው ለመስራት እንዲያስችላቸው ነው ብለዋል፡፡

ቀደም ባሉት የፈተና ተመዝጋቢዎች የምዝገባ ሂደቶች በርካታ ችግሮች እንደነበሩባቸውና እነዚህን የምዝገባ ስልቶች በየወቅቱ እያሻሻሉ ለመሄድ ጥረት ተደረጓል፡፡ በቅርብ ጊዜያቶች እንኳን ኤጀንሲው ለመቀያየር የሞከራቸው ፕሮግራሞችን ለመጥቀስ ያህል፡-
 በCOBOL ፕሮግራም በሚሠራበት ወቅት በአጠቋቆር ስህተት ምክንያት የሚፈጠሩ የስም፣ የትምህርት ቤት መለያ ኮድ፣ የትምህርት ዓይነት፣ የፆታ፣ የእይታ፣ የዜግነት፣ የመሳሰሉት ስህተቶች ፎርሙ ላይ በእጅ ከተስተካከሉ በኋላ በድጋሚ እንዲነበቡ ይደረጋል፡፡ ይህም ከፍተኛ የሰው ኃይል፣ የገንዘብና የጊዜ ብክነት ከማስከተሉም ባሻገር ሙሉ ለሙሉ ከስህተት የፀዳ ነበር ለማለት አይቻልም፡፡
 የምዝገባ ሲስተሙ ወደ ዳታቤዝ ከተቀየረ በኋላ እነዚህን ችግሮች በkey correction አሠራር ዘዴን በመጠቀም ሲባክን የነበረውን ከፍተኛ የሰው ኃይል፣ የገንዘብና የጊዜ ሀብት እንዲቀንስ አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ፕሮግራም ላይ ስህተቶች ሲፈጠሩ ለማረም የሚሠራው ሰው ስለሆነ አሁንም በምዝገባ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ሙሉ ለሙሉ ሊያስቀር አልቻለም፡፡ ስለሆነም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እንደአመቺነቱ Online Registration System ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

የኦንላይን ምዝገባ ስርዓት Web based appliction ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን ኢንተርኔትን በመጠቀም የተመዝጋቢዎችን ሙሉ መረጃ ከነፎቶግራፋቸው መዝግቦ በማዕከላዊ ሰርቨር ያስቀምጣል፡፡ ይህንን ሥርዓት (System) ለመጠቀም የምዝገባ ማእከሉ ኮምፒዩተር፣ ካሜራ (Webcam) እና ኢንተርኔት (Internet connection) ያስፈልጉታል፡፡ ምዝገባው የሚያከናወነው ትምህርት ቤቱ በሚወክለው ተወካይ (የIT ባለሙያ) ይሆናል፡፡ በOnline Registration System ላይ ምክክሮችና በአሰራር ሂደቱ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ከተካሄዱ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሀገር አቀፍ ፈተና ወሳጅ ተማሪዎች ያሏቸው ትምህርት ቤቶችና የምዝገባ ጣቢያዎች ምዝገባቸውን በOnline Registration System በማከናወን ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡