የሴቶች ቀን በኤጀንሲያችን ተከበረ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ107ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር ደረጃ ለ42ኛ ጊዜ ‹‹በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ንቅናቄ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን›› በሚል መሪ ቃል በትላንትናው ዕለት የተከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /march8/ በዛሬው ዕለት በኤጀንሲያችን በድምቀት ተከብሯል፡፡

በዓሉ በኤጀንሲው የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ሮ ትዕግስት አስማረ መክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን በቀጣይ ሴቶችን ማብቃት በሁሉም ዘርፍ ለሚታለመው ስኬት መሰረት መሆኑን በማውሳት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሄር ንግግር በማድረግ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት አካሂደዋል፡፡

በበዓሉ ላይ በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ የሥርዓተ-ፆታ አማካሪ የሆኑት አቶ ኤልያስ ጉዲሳ ሴቶች ለነጻነታቸው፣ ለእኩልነታቸው፣ ለሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውና ለፍትህ መከበርና መረጋገጥ ከአጋር ወንድሞቻቸው ጋር በጋራ ታግለው እውን ያደረጉት የመብት ጥያቄ በተመለከተና በሀገራችን ደረጃ በተጨባጭ የተመዘገቡ ስኬቶችን አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም የቀረበውን ሰነድ መሰረት ያደረገ ውይይት ከሰራተኞች ጋር ከተካሄደ በኋላ የፕሮገራሙ ፍጻሜ ሆኗል፡፡