የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይን የተጣለበት 7ተኛ ዓመት በኤጀንሲያችን ተከበረ

የህዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይን የተጣለበት 7ተኛ ዓመት በኤጀንሲያችን ተከበረ
በሀገራችን ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ ክንድ ግንባታው ሊጋመስ የቻለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት ሰባተኛ ዓመት በመላው ሃገሪቱ መከበሩን ተከትሎ በኤጀንሲያችንም እንዲሁ በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የሀገራችን ህብረ-ዜማ፣የህዳሴያችን ማማ!
ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የሀገራችን ህብረ-ዜማ፣የህዳሴያችን ማማ!በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኝው በዓል በኤጀንሲያችን በነበረው አከባበር የግድቡ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃና ህዝባዊ ተሳትፎው ባለፉት 7 ዓመታት ምን እንደሚመስል የሚያሳይ መረጃ የያዘ ሰነድ ለሰራተኛው ቀርቦ በቀጣይ ለግድቡ መጠናቀቅ ሁሉም ሰራተኛ ድጋፉን መቀጠል እንደሚገባው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የሀገራችን ህብረ-ዜማ፣የህዳሴያችን ማማ!