የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ፣ የገንዘብና የተለያየ ቁሳቁሶች ድጋፍ አካሄዱ
by
NEAEA
·
Published
· Updated
የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እና ለሀገር መከላከያ ደጀን ከመሆን ጋር በተያያዘ ውይይት አካሂደዋል። በቅርብ ጊዜ በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ለሚገኙ በጦርነቱ ለወደሙ የተለያዩ ት/ቤቶች የትምህርት ፈርኒቸሮችን ድጋፍ አበርክተዋል። በአሁኑ ወቅትም እንደሀገር ለ3ኛ ጊዜ የተከፈተብንን ወረራ በጀግንነት እየመከተ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊታችን የደም ልገሳ፣ የገንዘብና የተለያየ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል።
ይህ አስተዋጽኦም ጦርነቱ እስከቀጠለ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።